18.9 C
London
Sunday, June 1, 2025

አሞሪም የትላንት ምሽቱ ጨዋታ ለፍጻሜው ተጫዋቾችን ለመለየት እንደረዳቸው ገለጹ

- Advertisement -

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የትላንት ምሽቱ ጨዋታ ለዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የሚሰለፉትን ቋሚ አስራ አንድ ተጫዋቾች ለመለየት እንደረዳቸው ተናግረዋል።

አሞሪም “ጨዋታውን ብንሸነፍም ለዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ የሚሰለፉ ቋሚ አስራ አንድ ተጫዋቾችን መለየት እንድችል በጣም ጠቅሞኛል” ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ቡድናቸው የዩሮፓ ሊግ ዋንጫውን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር እንደሚያደርግ በመግለጽ ለፍጻሜው ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አሞሪም የቡድናቸው አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድ ጠንክሮ መስራት እና አሁንም ብዙ መሻሻል እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here