15.4 C
London
Sunday, June 1, 2025

አስደናቂ ዜና! አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት መንትያ ልጆችን በሰላም ተገላገለች!

- Advertisement -

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ወ/ሮ ደስታ ገጵ የተባሉ የጵላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ እናት በአንድ ጊዜ አራት መንትያ ህፃናትን በሰላም በቄሳሪያን ቀዶ ጥገና መውለዳቸውን የሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ወንድመነህ ካሳሁን ገልጸዋል።

ይህችው እናት ከዚህ ቀደም ሁለት መንትያ ልጆችን የወለዱ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በአንድ እርግዝና አራት መንትያ ህፃናትን በመውለድ በጋዘር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ክስተት ተመዝግቧል።

ዶክተር ወንድመነህ እንደገለጹት ህፃናቱ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አስፈላጊው የህክምና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል።

(ምንጭ: ጋዘር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል)

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here