የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ነገ የሚደረገውን የኤፌ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚፈልግ በግልጽ ተናግረዋል።
“ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን” ያሉት ጋርዲዮላ የኤፌ ካፕ ውድድር ለክለባቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም በፍጻሜው ጨዋታ ቡድናቸው የተሻለ አቋም እንደሚያሳይ እና ተጋጣሚያቸውን ክሪስታል ፓላስን ለመፎካከር ዝግጁ መሆኑን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የአማካይ ተጫዋቻቸው ሮድሪ በጉዳት ምክንያት በፍጻሜው ጨዋታ የመሳተፉ ጉዳይ አሁንም አጠያያቂ ነው። አሰልጣኝ ጋርዲዮላ ሮድሪ በሂደት ላይ መሆኑንና የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱን ቢናገሩም፣ ተጫዋቹን ለማሰለፍ የህክምና ቡድኑን ፈቃድ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል። “እሱን ለማሰለፍ አንቸኩልም” ሲሉ ጋርዲዮላ አክለዋል።