የሊቨርፑሉ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው አሌክሳንደር አርኖልድን ረስቶ በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ድል ደስታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
አርኔ ስሎት “ስለ አርኖልድ ማውራት የምናቆምበት ጊዜ አሁን ነው፤ በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ድላችን መደሰት አለብን” ብለዋል።
በዚህ የውድድር ዓመት ከሜዳቸው ውጪ ሊቨርፑልን ፈታኝ ቡድን የነበረው ማን እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ አርኔ ስሎት “ቼልሲ ነበር” ሲሉ መልሰዋል።
በተጨማሪም አርኔ ስሎት ስለ ዝውውር በተደጋጋሚ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ቅር መሰኘታቸውን ገልጸው “በጣም ያሳዝናል፣ ዓመቱን ሙሉ ስለ ኮንትራት ማራዘም ስጠየቅ ነበር። አሁን ደግሞ ስለሚመጡ ተጫዋቾች ጀምራችኋል። እኔ በይፋ ሳይጠናቀቅ ስለ ምንም ነገር መልስ አልሰጥም” ብለዋል።