“ግሬስ ቶርናመንት” የተሰኘው የእግር ኳስ ውድድር በግሬስ ክርስቲያን ሚዲያ አስተባባሪነት እንደሚዘጋጅ ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።
እንደተገለጸው “ግሬስ ቶርናመንት” ማህበረሰቡን ለስፖርት ለማነቃቃትና በመካከልም መቀራረብን በመፍጠር ስፖርታዊ ባህልን ለማዳበር ያለመ ነው።
በዚህ ውድድር 16 የእግር ኳስ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በሰላምና በፍቅር መንፈስ የወንጌልን ምሳሌ በመሆን ፉክክራቸውን እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
ይህ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በቡልቡላ ሜዳ ላይ የሚካሄድ ሲሆን በክብር እንግዶች የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ይገኛሉ። የመክፈቻ ጨዋታው በናዝራውያን ቡድን እና በዘጸአት ቤተ ክርስቲያን ቡድን መካከል እንደሚሆን ተገልጿል።