የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ተፎካካሪውን እስፓኞልን የሚያሸንፍ ከሆነ የላሊጋውን ዋንጫ ማሸነፉን በይፋ ያረጋግጣል። ክለቡ ዛሬ ምሽት ድሉን ካረጋገጠ በኋላ ነገ በከተማው ጎዳናዎች ላይ ደስታውን ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
እንደተገለጸው ባርሴሎና ዛሬ ምሽት የላሊጋውን ዋንጫ ካነሳ የሀገር ውስጥ ሶስትዮሽ (ኮፓ ዴል ሬይ፣ ሱፐር ኮፓ እና ላሊጋ) ዋንጫዎችን በአንድ ላይ በክፍት አውቶቡስ በመላው የባርሴሎና ጎዳናዎች በመዘዋወር ደማቅ ክብረ በዓል ለማካሄድ አቅዷል።
የአሁኑ የባርሴሎና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ቡድናቸውን በመምራት በዚህ አመት የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ እና ሱፐር ኮፓ ዋንጫዎችን ቀደም ሲል ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ሆኖም ባርሴሎና ዛሬ ምሽት የዋንጫ አሸናፊነቱን ማረጋገጥ ካልቻለ ወይም ክብረ በዓሉን በሌላ ምክንያት ማካሄድ ካልቻለ በዓሉ ወደሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ እንደሚዘዋወር ተገልጿል።