ሦስቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል። እነሱም፡
- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
- ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ
- ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ናቸው።
ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
(ምንጭ: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)