16.1 C
London
Monday, June 2, 2025

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰሌዳ ሌቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ

- Advertisement -

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከቆሙ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰሌዳ ቁጥሮችን በመፍታት የሚሸጡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ፖሊስ እንዳለው በረከት ማዕረጉ እና ሚኪያስ ባየልኝ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ለገሃር ግቢ ውስጥ በአጥር ዘለው በመግባት ከሁለት ተሽከርካሪዎች የፊትና የኋላ የሰሌዳ ቁጥሮችን ፈትተዋል። በወቅቱ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ሊይዟቸው ሳይችሉ አመልጠዋል።

ሆኖም በዚያች ሌሊት በአካባቢው በስራ ላይ የነበሩ የወንጀል መከላከል አባላት ሚኪያስ ባየልኝን ሲሮጥ በማግኘታቸው በቁጥጥር ስር ያውሉት ሲፈትሹትም የተሽከርካሪ ሰሌዳ አግኝተዋል። ፖሊስም ከሚኪያስ ባየልኝ ጋር በዚሁ ወንጀል ተሳታፊ የነበረውን በረከት ማዕረጉን በቀጣዩ ቀን በመያዝ ባደረገው ጥቆማ የሰረቃቸውን ሰሌዳዎች ከደበቀበት መኖሪያ ቤቱ ጣሪያ ላይ እንዲያመጣ ማድረግ ችሏል።

የፖሊስ ምርመራ ክፍል በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራውን እያጠናከረ ሲሆን ግለሰቦቹ አንዱን የሰሌዳ ቁጥር በ4 ሺህ ብር እንደሚሸጡ የምርመራ መዝገቡ እንደሚያመለክት ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ድርጊቶች በየጊዜው እየተለወጡ መምጣታቸውን ጠቁሞ በተለይም በከተማው የሚታዩ የዝርፊያና ሌሎች ወንጀሎች በተሰረቁ የሰሌዳ ቁጥሮች ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና መረጃ በመስጠት ረገድ ትብብሩን እንዲያጠናክር አሳስቧል።

(ምንጭ: የአዲስ አበባ ፖሊስ)

- Advertisement -
Latest news
- Advertisement -
Related news
- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here